የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ መርሐ-ግብር ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር ዓመት የጨዋታ መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
በዚሁ መሠረት የ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በፈረንጆቹ ነሐሴ 16 ቀን 2024 ማንቼስተር ዩናይትድ ከፉልሃም በሚያደርጉት ጨዋታ የሚጀመር ይሆናል፡፡
በሊጉ የመጀመሪያ ሣምንት ጨዋታዎችም÷ የ2023/2024 የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ይጠበቃል።
እንዲሁም÷ አርሰናል ከዎልቭስ፣ ዌስትሃም ከአስቶን ቪላ፣ ኢፕስዊች ከሊቨርፑል፣ ኤቨርተን ከብራይተን፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከቦርንመዝ፣ ኒውካስል ዩናይትድ ከሳውዛምፕተን፣ ሌስተር ሲቲ ከቶተንሃም፣ ብሬንትፎርድ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በመጀመሪያው ሣምንት ይፋለማሉ፡፡