Fana: At a Speed of Life!

በአንድ ቀን በደረሱ ሁለት የጀልባ አደጋዎች የ11 ስደተኞች ሕይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣልያን የባሕር ዳርቻ ትናንት በደረሱ ሁለት የጀልባ አደጋዎች ቢያንስ የ11 ስደተኞች ሕይዎት ሲያልፍ ከ60 የሚልቁት የደረሱበት አለመታወቁ ተሰምቷል፡፡

በላምፔዱሳ ደሴት አቅራቢያ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባጋጠማት የመስጠም አደጋ የ51 ተጓዦችን ሕይወት የታደገው የጀርመኑ በጎ አድራጎት ተቋም፥ በታችኛው የመርከቧ ወለል ላይ 10 አስከሬኖች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

እንዲሁም አንድ ስደተኛ ለጊዜው ከአደጋው ከተረፈ ከቆይታ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ነው ተቋሙ የገለጸው፡፡

አንደኛዋ ጀልባ ከሊቢያ ተነስታ÷ ከሶሪያ፣ ግብፅ፣ ፓኪስታን እና ባንግላዲሽ የመጡ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ እንደነበር በተባበሩት መንግስታት ሥር ያሉ የተለያዩ ድርጅቶች አስታውቀዋል፡፡

ሌላኛው ጀልባ ደግሞ በደቡባዊ ጣልያን ከምትገኘው ካላብሪያ የባሕር ዳርቻ በ125 ማይል ርቀት ላይ አደጋው እንዳጋጠማት ጠቅሰዋል፡፡

ከሁለቱም አደጋዎች እስከ አሁን ከ60 በላይ ሰዎች የት እንደገቡ አለመታወቁን ድንበር የለሽ የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን ገልጿል፡፡

ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ በባሕር ሲጓዙ የነበሩ ከ23 ሺህ 500 በላይ ስደተኞች ሕይወት ማለፉን እና የደረሱበት አለመታወቁን የመንግሥታቱ ድርጅትን መረጃ ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.