የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰመራ ከተማ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በአፋር ክልል ሰመራ እና ሎጊያ ከተሞች እየተከበረ ነው፡፡
በዓሉ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በአከባባር ሥነ-ሥርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡