የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በደሴና ወልድያ ከተሞች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በደሴ እና ወልድያ ከተሞች በተለያዩ ሃይማታዊ ሥነ-ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በደሴ እና ወልድያ ከተሞች ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሰባሰብ ሰላት በመስገድ እና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶችን በመከወን ነው በዓሉን እያከበረ የሚገኘው፡፡
በበዓሉ ላይ የተገኙት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ፥ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ሰላምን በማስጠበቅና በመረዳዳት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ም/ ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ እንድሪስ በሽር በበኩላቸው ፥ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከበር አንድነቱን በማስጠበቅ ሊሆን እንደሚገባ አንስተዋል።
በከድር መሃመድ