Fana: At a Speed of Life!

በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ክህሎት መር ተቋማዊ ግንባታ ማጠናከር ይገባል-አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ክህሎት መር ተቋማዊ ግንባታ ማጠናከር እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ፡፡

በክልሉ የስራና ክህሎት ቢሮ አጣዳፊ ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ ለክልል፣ ለዞን፣ ለወረዳ አመራሮች እና ለባለድርሻ አካላት የትውውቅ መድረክ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ÷በክልሉ በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ክህሎት መር ተቋማዊ ግንባታ ማጠናከር ይገባል።

በክልሉ ባሉት የተፈጥሮ ጸጋዎች ወጣቱን አስተባብሮ መስራት ከተቻል የኑሮ ውድነቱንም ሆነ የወጣቱን የስራ አጥነት ችግር ማቃለል እንደሚቻልም ገልፀዋል።

የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት አጣዳፊ እቅድ የተወሰኑ አካላት ብቻ በማካተት የማስተዋወቅ ስራ የተሰራ ቢሆንም ውጤቱ አመርቂ እንዳልነበር መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.