Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከበልግ እርሻ 28 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በበልግ እርሻ በዘር ከተሸፈነው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት 28 ሚሊየን ኩንታል ምርት የሚጠበቅ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ በበልግ ወቅት 1 ነጥብ 2ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን የተሳካ ስራ መሰራቱን የቢሮው ኃላፊ ጌቱ ገመቹ ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ወደ 28 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።

በተጨማሪም በክልሉ በመኸር እርሻ 10 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው፤ 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም እርሻ የሚለማ መሆኑን አመልክተዋል።

በመኸር ለማልማት ከታቀደው ውስጥ እስካሁን 9 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር ያህሉ ላይ የመጀመሪያ እርሻ የተከናዎነ ሲሆን ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር በላይ በዘር መሸፈኑን ነው የጠቆሙት።

የምስራቅ ቦረና ዞን አስተዳዳሪ አብዱልቃድር ሁሴን በበኩላቸው በዞኑ በበልግ እርሻ 130 ሺህ ሄክታር መሬት መልማቱን ጠቅሰው፤ ከዚህ ውስጥ 50 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የስንዴ ሰብል መልማቱን ተናግረዋል።

በዚህም ወደ 2 ነጥብ 5ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል፡፡

አካባቢው ከዚህ በፊት በድርቅ የሚጠቃ እንደነበረ አስታውሰው፤ አሁን ላይ ምርታማ እየሆነ ስለመምጣቱ ገልጸዋል።

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.