Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ያላትን ተሳትፎ ፈረንሳይ አደነቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ወታደራዊና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሌ/ጄ ኮል ኮምቤት የተመራ ልዑክ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከልንና የዓለም አቀፉ የሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋምን ጎብኝቷል፡፡

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በሰላም ማስከበር ተሳትፎ ያበረከተችው ጉልህ ተሳትፎና ሚና እንዲሁም በማሰልጠኛ ተቋሙ እየተከናወኑ ስላሉ የትምህርትና ስልጠና ሥራዎች በተቋሙ አመራሮች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የፈረንሳይ ወታደራዊና ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ሌ/ጄ ኮል ኮምቤት ኢትዮጵያ በአህጉርም ሆነ በዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ያላትን ተሳትፎ አድንቀዋል፡፡

በማሰልጠኛ ተቋሙ እየተከናወነ ያሉ ውጤታማ የትምህርትና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለማጠናከር ፈረንሳይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ መናገራቸውንም የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.