Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አባል የሆኑ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በቅርቡ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላም የጋራ ምክር ቤቱ አባላት ከአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ እየተሻሻለ የመጣውን የገዢ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ የመስራት አዲስ የፖለቲካ ባህል መዳበር የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን ከንቲባዋ በማበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

“በዚህ ዓመት ብቻ ስለከተማችን ሰላም፣ ልማት እና የፖለቲካ ባህል መዳበር ስንመክር ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው” ብለዋል ከንቲባ አዳነች።

ምንም እንኳን የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረንም፣ የጀመርነውን የትብብር ባህል በማጠናከር የጋራ አጀንዳዎቻችን ላይ ለጋራ ሀገር በጋራ መስራታችንን አሁንም እንቀጥላለን ሲሉም ገልፀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.