ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር ) እና ዶ/ር ደረጀ ድጉማ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታልን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር ) እና በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ የተመራ ቡድን የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል የስራ እንቅስቃሴን ጎበኘ።
በጉብኝቱ በክልሉ መንግስት በጀት እየተገነባ የሚገኘውን ሪጅናል ላቦራቶሪ፣ የህሙማን ልየታና ተኝቶ ህክምና፣ የእናቶችና ህጻናት ህክምና እና ተኝተው የሚታከሙ ህሙማን አገልግሎትን ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የማስተማሪያ ሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እርቅይሁን ጳውሎስ ገለጻና ማብራሪያ መስጠታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የፌደራል ጤና ሚኒስቴር አመራሮች፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አመራሮች፣ የሁሉም ክልሎች ጤና ቢሮ ኃላፊዎች እና የቤንች ሸኮ ዞን አመራሮችም በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።