ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የዶራሌ ሁለገብ ወደብ የገቢ-ወጪ ሂደትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በጅቡቲ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ አጠቃላይ የገቢ-ወጪ ሂደቱን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም ሚኒስትሩን ጨምሮ ፣አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ሌሎች የወደብ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና በጅቡቲ የኢትዮጵያ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።
ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በጉብኝታቸው÷ የአፈር ማዳበሪያን አስመልክቶ ወደ ሀገር ቤት የሚደረገው ዝውውር እንዲጠናከርና ሁለት አዳዲስ የማዳበሪያ ከረጢት መስፊያ ማሽኖች ወደ ኦፕሬሽን እንዲገቡ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከኢንባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የዶራሌ ሁለገብ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እና የሚወጡ አጠቃላይ ምርቶች የሚስተናገዱበት ወደብ ነው፡፡