Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝ በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ተግባራትን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንግሊዝ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የሽግግር ፍትሕ እና ሀገራዊ ምክክር ጥረቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የእንግሊዝ የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር ልዩ ልዑክ አሊሰን ብላክበርን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታና በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ዙሪያ ባሉ የሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ኦኮኖሚያዊ ልማት ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተለይም የእንግሊዝ መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት በዓለምአቀፉ ማህበረሰብ በኩል የሚደረጉ ጥረቶችን እንዲሁም ንግድና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ረገድ ማገዝ በሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ልዩ ልዑኳ÷ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የሽግግር ፍትሕ እና ሀገራዊ ምክክር ጥረቶችን የሀገራቸው መንግስት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.