Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው በማስተማር ውጤታማነት፣ ባሰተሟቸው ጥናታዊ ጹሁፎች፣ ለማህበረሰብ ባበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የተቋም አስተዳደር ድምር ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት፡-

ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል በሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ
ፕሮፌሰር አንተነህ በለጠ በፍርማሴዩቲክስ
ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በፕላንት ጄኔቲክስ
ፕሮፌሰር አህመድ ሁሴን በ አናሊቲካል ኬሚስትሪ
ፕሮፌሰር ታደሰ እጓለ በማይክሮባዮሎጂ
ፕሮፌሰር ተክለሀይማኖት ኃ/ሥላሴ በፕላንት ባዮቴክኖሎጂ
ፕሮፌሰር ተሾመ ሰንበታ በኮንደንስድ ማተር ፊዝክስ
ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት
ፕሮፈፌሰር ሀብቴ ተኪኤ በሜዲካል ኢንቶሞሎጂ
ፕሮፌሰር ቃላብ ባዬ በሂዩማን ኒውትሪሽን
ፕሮፌሰር ሰለሞን ሙሉጌታ በአርባን ፕላኒንግ
ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፍሰሀ በፖሊዮኢንቨሮመንታል ጥናት ናቸው።

ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ካደጉት መካከል ሁለት ሴት ምሁራን የሚገኙበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ‘ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ’ ለመደንገግ በወጣ አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረቡለትን የማዕረግ እድገት ማጽደቁን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.