የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ አጸደቀ፡፡
የሕዝብ በዓላት በሥነ-ምግባር የታነጻ ሀገር ወዳድ ማሕበረሰብ ለመገንባት ብሎም ለሀገርና ሕዝብ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ሕጋዊ ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተገልጿል፡፡
በዚህም የሕዝብ በዓላት የሚከበሩት በሀገር አቀፍ ደረጃ በመሆኑ እነዚህን ጉዳዮች የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ተፈጻሚነት ባለው ሕግ በአዋጅ እንዲወሰን ማድረግ ተገቢነት ያለው ስለሆነ አዋጁ መዘጋጀቱ ተብራርቷል፡፡
ነባሩ የሕዝብ በዓላት እና የዕረፍት ቀን መወሰኛ አዋጅ የሕዝብ በዓላት ሲከበሩ ጥቅም ሊያስገኙ በሚችሉ መልኩ በድምቀት የሚከበሩበትን ዝርዝር የአከባበር ሥነ-ሥርዓት አለማስቀመጡም ተመላክቷል፡፡
በየሻምበል ምኅረት