Fana: At a Speed of Life!

የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በትጋት መሥራት ይገባል- ድረስ ሳኅሉ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግጭት ምዕራፍን በመዝጋት የሕዝቡን የሠላም ፍላጎት እና የመልማት ጥያቄ ለመፍታት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳኅሉ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

“ዘላቂ ሰላምን በማጽናት በዘላቂነት እግር መትከል “በሚል መሪ ሐሳብ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ከሕዝብ ተወካዮች ጋር በደብረ ማርቆስ እየመከሩ ነው።

ድረስ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ባለፉት 10 ወራት በክልሉ የተከሰተውን የግጭት ምዕራፍ በመዝጋት የሕዝቡን የሰላም ፍላጎት እና የመልማት ጥያቄዎች ለመፍታት መሥራት ይገባል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሕዝቡን በማስተባበር ሰላምን ማረጋገጥ እና በጸጥታ ችግር ምክንያት የተጓተቱ ተግባራትን ለማነቃቃት በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባአሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.