Fana: At a Speed of Life!

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ከዩኒሴፍ እና ከዓለም ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ)ተወካይ አቡበከር ካምፖ (ዶ/ር) እና በዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

እንደሀገር በሚታዩ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የሀይል አቅርቦት ፍላጎቶችን ለማሟላት ተጨማሪ ሀብት ማፈላለግና ወደ ስራ መግባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በተለይ አሁን በአጋር አካላት ድጋፍ እየተተገበሩ ከሚገኙ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዜጎች የመጠጥ ውሃ እና የሳኒቴሽን አገልግሎት ፍላጎቶችን ታሳቢ ያደረገ የሃብት ማሰባሰብና ወደ ስራ መግባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል፡፡

በተጨማሪም በሂደት ላይ የሚገኙ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን ማጠናከርና አፈጻጸማቸውን ውጤታማ በማድረግ ሂደት ላይ መወያየታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያም ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከዩኒሴፍ እና ከዓለም ባንክ የተውጣጣ የቴክኒክ ቡድን ተቋቁሞ ሀብት ለማፈላለግ የሚያስችል እና በሂደት ላይ ያሉ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን ማሳለጥን ታሳቢ ያደረገ መነሻ ሀሳብና የድርጊት መርሃግብር እንዲያዘጋጅ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.