Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በጅግጅጋ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በጅግጅጋ እና ፋፈን ከተሞች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

አመራሮቹ በክልሉ መንግስት እና በባለሃብቶች የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን ነው ተዘዋውረው የተመለከቱት፡፡

በጉብኝቱ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ፥ በክልሉ ከለውጡ ወዲህ በምርትና ምርታማነት፣ በኢንቨስትመንት፣ በእንስሳት እርባታ፣ በኢንዱስትሪና በሌሎች የመሰረተ ልማት ዘርፎች የተሰሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.