Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በሃማስ ታግተው የነበሩ አራት ዜጎቿን አስለቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በፈረንጆቹ ካሳለፍነው ጥቅምት 7 ቀን ጀምሮ በሃማስ ታግተው የቆዩ አራት ዜጎቿን አስለቀቀች፡፡

እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ ባካሄደችው የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ ነው በሃማስ የታገቱ አራት ዜጎቿን ያስለቀቀችው፡፡

ሃማስ ከሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ አግቶ ወስዷቸዋል የተባሉት እስራኤላውያኑ÷ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተመላክቷል፡፡

በአንጻሩ ሃማስ የሚያስተዳድረው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፥ እስራኤል ለተልዕኮዋ ስትል ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ዜጎች ለሕልፈት መዳረጋቸውን አስታውቋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ሕይወት ለማትረፍም ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ መገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.