ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የስራ ኮንፈረንስ ምክትል የበላይ አካል ሆና ተመረጠች On Jun 7, 2024 76 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የሰራተኛ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2024 እስከ 2027 ድረስ ምክትል የበላይ አድርጎ መርጧል፡፡ ምርጫው የተካሄደው ዛሬ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ባለው 112ኛው የዓለም የስራ ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡ ጉባኤው 18 መደበኛ አባላትን እና 28 ምክትል አባላትን የበላይ አካል አድርጎ የመረጠ ሲሆን፥ ለአፍሪካ ሀገራት 13 መቀመጫዎች መሰጠቱን በጄኔቫ ከኢፌዴሪ ቋሚ ተጠሪ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ 76 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint