Fana: At a Speed of Life!

አቶ እንዳሻው ጣሰው ከቀቤና ብሔረሰብ ተወላጅ አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በየደረጃው ከሚገኙ የቀቤና ብሔረሰብ ተወላጅ አመራሮች ጋር መክረዋል።

በውይይታቸውም ፥ በልዩ ወረዳው ያለውን የሠላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጅምር ስራዎችን በማጠናከር የብሔረሰቡን ተወላጅ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በማምጣት በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

በውይይቱ ከፌዴራል እስከ ወረዳ ደረጃ የሚገኙ የብሔረሰቡ ተወላጅ አመራሮች መሳተፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.