ከአጠቃላይ ሟቾች መካከል የ46ቱ ሕይወት ያለፈው በግንቦት ወር ብቻ መሆኑን ሂንዱስታን ታይምስ ጋዜጣን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በሌላ በኩል በሕንድ ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 እስከ አሁን 24 ሺህ 849 ሰዎች ከሙቀት መጨመር ጋር በተያያዘ የጤና ዕክል እንዳገጠማቸው ዘገባው አመላክቷል፡፡
በዚህ ዓመት ሕንድ ከባድ የሙቀት መጠን እንዳጋጠማት የተገለጸ ሲሆን÷ ለአብነትም በተለያዩ አካባቢዎች ከ45 እስከ ከ50 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ የሆነ የሙቀት መጠን መመዘገቡ ተጠቅሷል፡፡