አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ጋር ተወያዩ On May 31, 2024 118 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሳዓድ ሙባረክ ሳዓድ አል ጃፋሊ አል ናኢሚን ጋር ተወያዩ። በውይይታቸውም፤ የኢትዮ-ኳታር የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽንን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም የሀገራቱን ትብብር ለማሳደግ በዚህ ዓመት የፖለቲካ ምክክር ለማካሄድ ተስማምተዋል። በዚሁ ወቅት አምባሳደር ሳዓድ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተላከ መልዕክት ለአምባሳደር ታዬ ማስረከባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። 118 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint