Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 124 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 124 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር ከተመለሱት ውስጥ ዘጠኙ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ34 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.