Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ የህፃናት መረጃ አያያዝ ስርዓት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የህፃናት መረጃ አያያዝ ስርዓት በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡

የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ በተቋማት መካከል አገልግሎት ለሚፈልጉ ህፃናት ቀልጣፋ የቅብብሎሽ ስርዓት እንዲኖር፣ አገልግሎት የሚሹ ህፃናትን ምስጢር ለመጠበቅ፣ ግላዊነትና ከተጨማሪ ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም የነበረውን የወረቀት መረጃ አያያዝ ወደ ዲጂታል ለመቀየር የሚያስችል እንደሆነም ተመላክቷል።

የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ይፋ ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ቀደም ሲል የነበረው የመረጃ አያያዝ የህፃናትን ደህንነት ከመጠበቅ አንጻር ክፍተት እንደነበረበት አስታውሰዋል።

ክፍተቶችን ለማስወገድና ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ሲባል ይህ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ይፋ እንደተደረገ ተናግረዋል።

ሁሉንም ህፃናት በተለይ ደግሞ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማረጋገጥና የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም አስገንዝበዋል።

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.