አፍሉዌንስ የተባለው የቻይና ኩባንያ ምርት ማምረት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሉዌንስ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ የቅድመ ኦፕሬሽን ስራዎችን አጠናቆ ምርት ወደ ማምረት መሸጋገሩን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
ኩባንያው ከኮርፖሬሽኑ ጋር የውል ስምምነት ፈፅሞ በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ የቅድመ ኦፕሬሽን ስራዎችን ሲያከናው መቆየቱ ተገልጿል።
ከ725 ሚሊየን ብር በላይ ኢንቨስት ያደረገው አፍሉዌንስ ኩባንያ፤ የተለያዩ ትራንስፎርመሮችንና ዲጂታል ቆጣሪዎችን በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርብ መሆኑ ተነግሯል።
የኩባንያው ምርት በኢትዮጵያ ያለውን የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
5 ሺህ 500 ካሬ ሜትር የማምረቻ ሼድ ተረክቦ ወደ ስራ የገባው ኩባንያው፤ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ከ300 በላይ የስራ እድልን እንደሚፈጥር መገለጹን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡