Fana: At a Speed of Life!

የስፖርት መሰረተ-ልማት ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው

አዲስ በባ፣ ግንቦት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፖርት መሰረተ-ልማት ኢንቨስትመንትን በየዓመቱ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ፡፡

ሚኒስቴሩ ከክልልና ከተማ አሥተዳደሮች እና ከሀገር አቀፍ የስፖርት ማኅበራት አመራሮች ጋር እየመከረ ነው፡፡

አቶ ቀጄላ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ መንግሥት የስፖርት ዕድገቱን ለማፋጠን የሚረዳ ፖሊሲ ከማውጣት ጀምሮ ማኅበራትን በተለያዩ መንገዶች ለመደገፍና የስፖርት መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንትን በየዓመቱ ለማሳደግ ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ማኅበራት ዓላማቸውን እንዲያሳኩ መልካም ስፖርታዊ አሥተዳደር መስፈን እንዳለበት ዓለም አቀፍ ተሞክሮች ጭምር ያስረዳሉ ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ቀደም ሲል ከሚስተዋሉ የዘርፉ ችግሮች መካከልም÷ አድሎአዊነት፣ የሥነ-ምግባር፣ የማጭበርበር እና ያልተገባ የሰውና የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም ጠንካራ የስፖርት ማኅበራት አለመኖር እንደሆኑም ጠቅሰዋል፡፡

እነዚህ ችግሮች በሀገራችን በምን ያህል ደረጃ እንዳሉ በጥናት የተደገፈ መረጃ ማቅረብ ባይቻልም ችግሮቹ እንዳሉ ግን ይታመናል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.