Fana: At a Speed of Life!

የምክክር ኮሚሽኑ ዓላማ እንዲሳካ ድጋፍ እናደርጋለን- ምክር ቤቶች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በተለያዩ ክልሎች በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች አስታወቁ፡፡

በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች የሕዝብ ውክልናን ይዘው እንደመሥራታቸው ለሕብረተሰቡ አብሮነት በትኩረት እንደሚሠሩ የአማራ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች አፈ-ጉባዔዎች ገልጸዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቡቶ አኒቶ÷ ኢትዮጵያ ብዝኃ-ማንነት ያላት መሆኗ በመግለጽ ልዩነቶችን ተቀብሎ በሰላምና በትብብር ለመኖር ውይይት ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

በጋራ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ልዩነቶችን መፍታት የጋራ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ በመሆኑ ምክር ቤቶች የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ አማረ ሰጤ በበኩላቸው ጠቃሚ ሀገራዊ እሴቶችን በትምህርት ካሪኩለም ቀርጾ ማስተማር የጋራ ትርክትን ለመፍጠር ወሳኝ ሚና አለው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ መሰለ ከበደ ÷ ጠቃሚ እሴቶች ለትውልድ እንዲተላለፉ፣ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ምክር ቤቶች ሚናቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የተለያዩ ክልሎች ምክር ቤቶች ጠቃሚ እሴቶች ለትውልድ እንዲተላለፉና የሕብተረሰቡን አብሮነት የሚያጠናክሩ የጋራ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሠሩ መሆኑንም አፈ-ጉባዔዎቹ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.