የኢትዮ- ጅቡቲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ በጅቡቲ በተካሄደው 16ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ላይ የሀገራቱን የንግድ ግንኙነት አስመልክቶ በተነሱ ነጥቦች ላይ ለመወያየት ያለመ መድረክ ዛሬ ተጀምሯል።
በውይይቱ ላይ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ የተመራ ልዑክ ተሳትፎ እያደረገ ነው፡፡
የጅቡቲ የንግድ እና ቱሪዝም ዋና ጸሐፊ አሊ ዳውድ፣ የጅቡቲ ንግድ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ሌሎች ዲፕሎማቶች በመድረኩ ተሳትፈዋል።
በመድረኩ በሀገራቱ መካከል ስላለው የንግድ ማዕቀፎች፣ በሕገ ወጥ የድንበር ንግድ እንዲሁም በ2023 የንግድ ቴክኒካል ኮሚቴ በተለዩ ነጥቦች ውይይት መደረጉ ተገልጿል።
በተጨማሪም ውይይት በተደረገባቸውና ቀጣይ ትኩረት በሚሹ አጀንዳዎች ዙሪያ ከሁለቱም አካላት የሚመለከታቻው የመንግስት ተቋማት ተገናኝተው በመወያየት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው መግባባት ላይ መደረሱን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡