የመንግሥትና የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶች የወጣቶች ፎረም ምስረታ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቶችን፣ የወጣት አደረጃጀቶችን እና በወጣቶች ዙሪያ የሚሰሩ ባለ ድርሻ አካላትን ያቀፈ የመንግሥትና የሲቪክ ማኅበራት ድርጅቶች የወጣቶች ፎረም ምስረታ እየተካሄደ ነው፡፡
ምስረታውን እያካሄደ ያለው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡
ፎረሙ በመንግሥት በወጣት አደረጃጀቶች፣ በወጣቶች እና ባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የወጣቱን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዲዔታ ሙና አሕመድ በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ወጣቶች ሩቅ ዓላሚዎች እና የሀገር የጀርባ አጥንቶች በመሆናቸው ጥራት ያለው ትምህርት እና አስተማማኝ የጤና አገልግሎት ሊያገኙ ይገባል ብለዋል፡፡
የፎረሙ ምስረታም ባለድርሻ አካላትን በቅንጅት እንዲሰሩ በማድረግ ውጤታማ የሆኑ ወጣቶችን ማፍራት ያስችላል ነው ያሉት።
የፎረሙ አወቃቀር ወጣቶች መረጃ የሚያገኙበት፣ ድምፃቸውን የሚያሰሙበት፣ ኃላፊነት የሚወስዱበት እንደሚሆንም ተገልጿል።
በትዕግስት አስማማው