Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን መስኮች ተሞክሮዋን አጋራች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን መስኮች ያላትን ተሞክሮ በጋና በተካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ሚዲያ ኮንቬንሽን ላይ ማጋራቷን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኮፎ አዶ በተገኙበት በአክራ በተካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ሚዲያ ኮንቬንሽን ላይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን መስክ የኢትዮጵያን ልምዶች አቅርበዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን በማድረግ ለዘርፉ የሰጠችውን ትኩረት አብራርተዋል።

በተጨማሪም በሰው ሠራሽ አስተውሎት መስክ በተለይም የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትና ጉዳት መከላከል ላይ የጀመረቻቸውን ተግባራትም ገልጸዋል፡፡

አፍሪካ የራሷን ታሪክ በራሷ አንደበት መናገር እንድትችልም ሀገር በቀል ቋንቋዎቿን በቴክኖሎጂ ማበልፀግ እንደሚገባት ሚኒስትር ዴዔታዋ አስገንዝበዋል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ አማርኛን ጨምሮ የተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን ለኮምፒውተር የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እንዳላት አስታውቀዋል፡፡

ይህ ጅምር በሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ሊሰፋ እንደሚገባው አመላከተው የአፍሪካን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ለማሳየት ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት ኮንቬንሽኑ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ መጤቃቸውን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.