በአማራ ክልል 20 ሺህ ሔክታር አሲዳማ አፈር ለማከም እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት 20 ሺህ ሔክታር አሲዳማ አፈር ለማከም እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ም/ሃላፊ ቃልኪዳን ሽፈራው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ በክልሉ 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር መሬት አሲዳማ እና ከፊል አሲዳማ ነው።
ምርታማነትን ከ50 በመቶ አስከ መቶ በመቶ የሚያጠፋውን አሲዳማ አፈር ማከም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ከሚታረሰው 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሔክታሩ በጠንካራ አሲድ መጠቃቱን ጠቁመው÷ ይህም 78 ከመቶ መሆኑን አመልክተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት 20 ሺህ ሄክታር አሲዳማ አፈርን ለማከም ለተያዘው እቅድ 600 ሺህ ኩንታል ኖራ መዘጋጀቱንም አንስተዋል፡፡
በእሸቱ ወ/ሚካኤል