Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ ለአርቲፊሻል አስተውሎት ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት እንድትሰጥ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ትክክለኛ ድምጿን እንድታሰማ የአፍሪካ ሀገራት ለአርቲፊሻል አስተውሎት ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ፡፡

የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ መሪዎችና ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ላይ የሚመክረው 3ኛው የአፍሪካ ሚዲያ ኮንቬንሽን በጋና አክራ እየተካሄደ ይገኛል።

አፍሪካዊ መረጃዎችን ለአርቴፍሻል አስተውሎት ግብዓት በሚሆን መልኩ በማዘጋጀትና የአህጉሪቱን መጪ የቴክኖሎጂ ጉዞ በማፋጠን በኩል ሚዲያው ከፍተኛ ሚና እንዳለው በጉባኤው ተነስቷል።

የዘንድሮው ጉባኤ የሚዲያ ነፃነትና የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም ሚዲያውን በኢኖቬሽንና በአርቲፊሻል አስተውሎት የማገዝ አጀንዳዎችን ይዟል።

በተጨማሪም÷ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ሀገራት የሚወስዱትን መፍትሔ በተመለከተ ለብዙሃኑ መረጃ የማድረስ ሃላፊነታቸውን ሚዲያዎች እንዲወጡ ማድረግ ላይም ጉባኤው ይመክራል።

ለሁለት ቀናት ቀጥሎ በሚካሄደው ጉባኤ ኢትዮጵያ በተለይ በአርቲፊሻል አስተውሎት እንዲሁም በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፎች የምታከናውናቸውን ተግባራት በተመለከተ ልምዷን እንደምታካፍል ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.