የሥራ ከባቢን ምቹ ማድረግ ከቀዳሚ የትኩረት መስኮች አንዱ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) On May 15, 2024 261 አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥት ቢሮዎች የቢሮ ከባቢን መቀየር የሥራ ከባቢን ምቹ ማድረግ ከቀዳሚ የትኩረት መስኮች አንዱ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ምድረ ግቢ የተሰሩት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም ሚኒስቴሩ በከተማ ልማት ሥራ አኳያ ያሉትን ርምጃዎች መጎብኘታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ በዚህ ወቅትም የመንግሥት ቢሮዎች የቢሮ ከባቢን መቀየር የሥራ ከባቢን ምቹ ማድረግ ከቀዳሚ የትኩረት መስኮች አንዱ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡ 261 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint