Fana: At a Speed of Life!

የኢትየጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህጋዊ ሰውነት በማግኘቱ ምስጋናውን አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የኢትየጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህጋዊ ሰውነት በማግኘቱ ምስጋና አቀረበ።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትላንት ባካሄደዉ 16ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ አዋጅን መርምሮ ማጽደቁ ይታወሳል።

ምክር ቤቱን ህጋዊ ሰውነት የሚያሰጠው አዋጅ እንዲጸድቅ መደረጉም ለአመታት የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ ሆኖ በመቆየቱና ምላሽ እንዲያገኝ ያስቻለ ነው ሲሉ በርካቶች እርምጃውን አወድሰውታል።

የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ ለምስጋና በተዘጋጀው መግለጫ ላይ ጥያቄው ለበርካታ ዓመታት ሲንከባበል የቆየ መሆኑን አንስተዋል።

“የቀድሞ የመጅሊሱ መሪ የነበሩት ሀጅ መሀመድ ሳኒ ሀቢብ፣ እኔን ጨምሮ በርካቶች ታግለውበታል፣ ክርስትያን ወገኖቻችንም ጨምሮ” ብለዋል።

ለዚህ በመብቃቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን በመላው ሙስሊም ስም ላመሰግን እወዳለሁ ነው ያሉት።

“ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ ያፀደቀው ምክር ቤቱንም እና ተቋማዊ አንድነትን ለመፍጠር የተቋቋመው የ11ዱ አባላት ኮሚቴም ምስጋና ይገባቸዋል” ብለዋል።

የሚወክለው ተቋምም ህጋዊ ሰውነት በማግኘቱ መላው ሙስሊም እንኳን ደስ አለህ ለማለት እፈልጋለሁ  ነው ያሉት።

ተቋሙ ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረዉ ሲለፉና ሲደክሙ ለቆዩ አካላትም ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል፤ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ።

ከለዉጡ በፊት ጠንከር ብለዉ ሲጠየቁ ከነበሩ ጥያቄዎች ማካከል አንዱ የዚሁ ተቋማ ህጋዊ ሰዉነት የማግኘት ጉዳይ አንዱ ሲሆን፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቀራራቢነት ህዝበ ሙስሊሙ ተቋማዊ አንድነትን ለማምጣት ካካሄደዉ መቀራረብ በኋላም ህጋዊ ሰውነት የማግኘቱ ጉዳይ መልስ ያገኛል ተብሎም ሲጠበቅ ቆይቷል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.