በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት ተፈጸመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የ2016 ኤክስፖ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መፈፀሙን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።
ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ታምርት የ2016 ኤክስፖ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኤክስፖው የተለያዩ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነበር።
በኤክስፖው ከ100 ሺህ በላይ ግለሰቦችና ተቋማት መሳተፋቸውን ጠቁመው ÷ከ57 ሀገራት የመጡ ድርጅቶች እና 157 ዲፕሎማቶች መገኘታቸውንም ጠቅሰዋል።
በኤክስፖው በአጠቃላይ 210 አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉ ሲሆን÷ በዚህም 8 ሺህ 188 አይነት ግብይት ተፈጽሞ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መከናወኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡