የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የችቦ ማብራት ፕሮግራም በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያ ትወዳዳር፣ ተወዳድራም ታሸንፍ” በሚል መሪ ሀሳብ የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የችቦ ማብራት ፕሮግራም በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የፓሪስ ኦሎምፒክ የችቦ ማብራት ፕሮግራም ቀደም ሲል በመቀሌ፣ በደሴ፣ በሰመራ እና በቢሾፍቱ ከተሞች መካሄዱ ይታወሳል፡፡