በዶሃ የዳይመንድ ሊግ 3 ሺህ መሰናክል የሩጫ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በቀዳሚነት አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዶሃ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ 3 ሺህ መሰናክል የሩጫ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በቀዳሚነት አጠናቀቀ።
አትሌቱ ውድድሩን 8:07.25 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው ውድድሩን ያሸነፈ ሲሆን፤ ኬንያዊው አትሌት ኪበብዎት አብራሃም 8:07.38 እንዲሁም አትሌት ጌትነት ዋለ 8:09.69 በሆነ ጊዜ በመግባት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል።
በተመሳሳይ በ5 ሺህ ሴቶች 14:26.98 በሆነ ጊዜ በመግባት ኬንያዊቷ አትሌት ቼቤት ቤአትሪስ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደግሞ ከሁለተኛ እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል።