በከተማዋ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሲካሄድ የነበረው የትራንስፎርሜሽናል እቅድ ዝግጅት ወርክሾፕ ሲጠናቀቅ ከንቲባዋ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲያስችል በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ መስራት ይገባል።
ይህም በስራ እድል ፈጠራ፣ በቤቶች አቅርቦት፣ በመሬት ልማትና አስተዳደር፣ በገቢ አሰባሰብ እና በትራንስፖርት ለውጥ አምጪ የሆኑ ግቦች ላይ በተደረገው ውይይት በቀጣይ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚጠበቅ አንስተዋል፡፡
ከንቲባዋ አክለውም ከወርክሾፑ በተገኘው ግብዓት፣ በተደረሰበት ተግባቦት ልክ እና ለመራጩ ህዝብ በተገባው ቃል መሰረት ጥያቄዎችን ለመመለስ በቀጣይ ድጋፍ እያደረጉ ካሉ ባለድርሻ አካላት፣ ከከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ለውጤታማነቱም ያለ እረፍት መታገል ይገባል ማለታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡