ጥንቃቄ የሚሻው የበዓል ወቅት አመጋገብ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የበዓላት ወቅት አመጋገብ ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገበት ለጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል፡፡
የጾም ቀናትን መጠናቀቅ ተከትለው በሚመጡ በዓላት ያለውን አመጋገብ ጥንቃቄ የተሞላበት ማድረግ እንደሚገባም ነው ባለሙያዎች የሚመክሩት፡፡
ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ከቅባት ርቆ የቆየ ጨጓራ ለህመም የመዳረግ ዕድሉ ከፍተኛ ስለሚሆን ነው ይላሉ፡፡
ጥንቃቄ የጎደለው አመጋገብ ከሆነ÷ እንደ ሆድ መንፋት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጨጓራ ማቃጠል እና ሌሎች ህመሞችንም ሊያስከትል ይችላል ይላሉ፡፡
በመሆኑም በዓላትን የጤና መታወክ ሳያጋጥም ለማሳለፍ÷ የሚዘጋጀው ምግብ ንጽህናው እንዲጠበቅ እንዲሁም ምግቦች ቅባት የበዛባቸው እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
በአመጋገብ ወቅትም ቀስበቀስ ጨጓራን በማላመድ መሆን እንዳለበት ነው የሚመክሩት፡፡
ጣፋጭ ምግቦችን እና የአልኮል መጠጦችን ከልክ በላይ ባለመውሰድ እራስን እና ቤተሰብን ከህመም መጠበቅ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡