Fana: At a Speed of Life!

የኢየሱስ ክርስቶስ የስቀለት በዓል በዓለም ዙሪያ…

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት በሐይማኖታዊ አስተምኅሮዎችና ሥርዓተ-ክዋኔዎች ይከበራል፡፡

ዕለቱ ከሚከበርባቸው በርካታ ሀገራት መካከልም÷ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሩሲያ፣ ግብጽ፣ ግሪክ፣ እስራኤል፣ ቡልጋሪያ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

በዓሉ የሚከበረውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አማኞች ዘንድ ነው፡፡

የአከባበር ሁኔታው እንደየ ሀገራቱ እና ሐይማኖቱ ቢለያይም÷ በአብዛኛው ምዕመናን ዕለቱን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተቀበለውን ስቃይ እና ህማም እያሰቡ በጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት እና ዝማሬ ማሳለፍ የተለመደ ነው፡፡

ለምሳሌ በግብጽ ኮፕቲክ ቤተ-ክርስቲያን የክርስቶስን መስቀል ተሸክሞ በመጓዝ ስቃይና መከራ እንደተቀበሉ በማሰብ በፀሎት ሲያስቡ÷ በግሪክ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት እና ያገኘውን መከራ በሚያሳይ መልኩ ያከብራሉ፡፡

እንዲሁም በእስራኤል ኢየሱስ ክርስቶስ ለስቅላት ወደ ጎለጎታ ተወስዶበታል ተብሎ በሚታመነው ስፍራ ክርስቲያኖች ተሰባስበው አንዳንዶችም መስቀል ተሸክመው በመጓዝ ያከብራሉ፡፡

በአብዛኛው የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን የስቅለት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያሳየውን ወሰን የሌለው ፍቅር በማሰብ በተውኔት መልክ በመጫወትና በጎዳናዎች በመጓዝ ጭምር ያከብራሉ፡፡

በበቡልጋሪያም ስቅለትን ክርስቲያኖች በመጸለይ ሲያከብሩ÷ በሀገሪቱ የመንግሥትና የንግድ ድርጅቶች ዝግ ይሆናሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.