Fana: At a Speed of Life!

ክልሉ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ926 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ926 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ።

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ እሸቱ ጎዴቶ እንደገለጹት÷ የክልሉ የይቅርታ ቦርድ በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ታራሚዎችን ከመንግስት፣ ከህዝብና ከታራሚ ጥቅም አኳያ ሲመረምር ቆይቷል።

በተደረገው ምርመራም በአጠቃላይ የይቅርታ ጥያቄ ካቀረቡ 978 ታራሚዎች መካከል መስፈርቱን ያሟሉ 926 ታራሚዎች ጥያቄያቸው ለክልሉ መንግስት ቀርቦ የይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል።

የይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል 920 ታራሚዎች ከእስር የሚለቀቁ ሲሆን÷ስድስቱ ደግሞ የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው ናቸው።

ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት በነበራቸው ቆይታ በአግባቡ ስለመታረማቸው፣ ስለመታነጻቸውና ስለመልካም ባህሪያቸው ምስክርነት የተሰጠባቸው መሆኑንም አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.