Fana: At a Speed of Life!

በሻምፒየንስ ሊጉ ግማሽ ፍፃሜ ዶርትመንድና ፓሪስ ሴንት ጀርሜይን ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ ቦርሺያ ዶርትመንድና የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርሜይን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያካሂዳሉ፡፡

ጨዋታው ከምሽቱ 4 ሰዓት በዶርትመንድ ሜዳ ሲገናል ኤዱና ፓርከ የሚካሄድ ሲሆን÷ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በፓሪስ ፓርክ ደ ፕሪንስ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ትናንት ባየርን ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ በአሊያንዝ አሬና ያደረጉት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

የባየርን ሙኒክን ግቦች ሌሮይ ሳኔ እና ሀሪ ኬን ሲያስቆጥሩ÷ የሪያል ማድሪድን ግቦች ደግሞ ቪኒሽየስ ጁኒየር ከመረብ አሳርፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.