Fana: At a Speed of Life!

ከ80 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለሚያደርግ የውሃ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሃዋሳ ከተማ ከ80 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ ተግባራዊ ከሚደረጉ ፕሮጀክቶች አንዱ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ነው።

ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የፋራ ሂጠታ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትም የሃዋሳ የከተማን የውሃ ሽፋን እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል፡፡

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በበኩላቸው÷ የከተማዋ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 80 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

የሂጠታ ፋራ የውሃ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅም የውሃ ሽፋኑን 84 በመቶ እንደሚያደርሰው ጠቅሰው÷ለፕሮጀክቱ ግንባታ 230 ሚሊየን ብር መመደቡን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከ6 እስከ 9 ወራት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.