Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ቢያንስ የ32 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ በተከሰተውና የሀገሪቱን ሰፊ ግዛት ባካለለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ቢያንስ የ32 ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሁለት ሰዎች ደግሞ መጥፋታቸው ተነግሯል፡፡

በጎርፍ አደጋው 103 ሺህ 500 ሰዎችለጉዳት መጋለጣቸውም ተጠቁሟል።

በኬንያ ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ ከባድ ዝናብ እየጣለ ቢሆንም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ዝናቡ ተባብሶ በመቀጠሉ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ማስከተሉን ሲኤንኤን ዘግቧል።

በዚህም በሀገሪቱ ዋና ከተማ ናይሮቢ ችግሩ የተባባሰ ሲሆን አንዳንድ መንገዶች ከትናንት ጀምሮ በጎርፍ ምክንያት መዘጋታቸው ተጠቁሟል።

ዝናቡ በመቀጠሉ በናይሮቢ የጎርፍ መጥለቅለቁ ያስከተለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉን ያመለከተው ዘገባው፤ አደጋው በሰው ህይወትና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የአስቸኳይ ጊዜ የህይወት አድን ስራ መሰራት እንዳለበት መጠየቁን አመልክቷል።

እስካሁን የጎርፍ አደጋው ባስከተለው ጉዳት ቢያንስ 32 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ እና ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ለመሸሽ መገደዳቸውን ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.