Fana: At a Speed of Life!

የቫይታሚን ዲ እጥረት የሚያስከትለው ጉዳት

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቫይታሚን ዲ ለአጥንት መስሪያ የሚያገለግለውን ንጥረ ነገር ወደ አጥንት እንዲጓጓዝ የሚያግዝ ነው።

ካልሺየም ከምግብ ውስጥ አንጀትን አልፎ ወደ ደም እንዲገባ የሚያደርግ ለአጥንት መጠንከር በጣም ወሳኝ ሚና የሚጫወትም ነው።

ቫይታሚን ዲ ከምግብ የሚገኝ ሲሆን÷ ዋና መገኛው ግን የፀሐይ ብርሐን ነው።

ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል ማለትም (ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ አዛውንቶች) በቫይታሚን ዲ እጥረት ሊጠቁ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

በአብዛኛው የከተማ ነዋሪዎች ፀሐይ የመሞቅ ልምዳቸው ዝቅተኛ ስለሆነ ለቫታሚን ዲ እጥረት የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ መሆኑንም የህክምና ባለሙያዎች ይጠቁማሉ፡፡

የቫይታሚን ዲ እጥረት ደግሞ ከወገብ ህመም፣ ከነርቭ ህመም፣ ከጡንቻ መዛልና መልፈስፈስ እስከ ከባዱ የእንጎልና አዕምሮ ህመም (አልዛይመር፣ መልቲፕል እስክለሮሲስ እና ድባቴ) እንደሚዳርግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ቫይታሚን ዲ አጥንትን ያጠነክራል፣ የጡንቻ ጤንነትን ይጠብቃል፣ የጀርባ አጥንትን በማጠንከር በውስጡ የሚያልፉትን ህብረሰረሰርና የነርቭ ዘንግን ከጉዳት ይከላከላል፤ የበሽታ መከላከያ ስርዓትን አደራጅቶ ከህመም ይታደጋል።

የጠዋት ወይም ደግሞ የማታ ፀሐይ ቢያንስ ለግማሽ ሰዓት ያለ ልብስ እና ያለ ቅባት የሰውነት ቆዳን ቢያንስ በሳምንት አራት ቀን በመሞቅ ከፀሐይ ማግኘት ያለብዎትን ምግብ ማግኘት ይችላሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.