በማንዴላ መታሰቢያ ውድድር ውጤት ላስመዘገበው ቡድን አቀባበል ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ የማንዴላ መታስቢያ ውድድር ላይ በመሳተፍ ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ ቦክስ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሀገሩ ሲመለስ አቀባበል ተደረገለት።
ቡድኑ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ ቢልልኝ መቆያ እንዲሁም የቦክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ በውድድሩ ላይ በ 54 ኪ/ግ በሱራፌል አላዩ፣ በ60 ኪ/ግ በሚሊዩን ጨፎ፣በ66 ኪ/ግ ቤተል ወልዱ የብር ሜዳሊያ ሲያስመዘግብ በ50 ኪ/ግ ቤተልሄም ገዛህኝ፣ በ54 ኪ/ግ ሮማን አስፋ እና በ75 ኪ/ግ በተመስገን ምትኩ የነሃስ ሜዳሊያ በማሸነፍ ውድድሩን አጠናቋል።