የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከዓለም ዓቀፍ የብሪክስ የፀረ-ሙስና ቡድን ጋር ውይይት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን ከዓለምዓቀፍ የብሪክስ የፀረ-ሙስና ቡድን ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡
ውይይቱ በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
የውይይት መድረኩ ነገን ጨምሮ የሚካሄድ ሲሆን፥ በፀረ-ሙስና ትብብር ዙሪያ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡