የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ከባየርንሙኒክ እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
ባየርንሙኒክ ከአርሰናል በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ በአርሰናል በኩል ማርቲን ኦዲጋርድ እና ቡካዮ ሳካ በጉዳት ምክንያት መሰለፋቸው አጠራጣሪ ሲሆን፤ የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ጁሊያን ቲምበር በጉልበት ጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
በባየርንሙኒክ በኩል አልፎንሶ ዴቪስ ከጨዋታው ውጭ መሆኑ ሲረጋግጥ ስርጂ ጊናብሪ፣ ሌሮይ ሳኔ እና ኬንግስሌይ ኮማን የመሰለፋቸው ጉዳይ አጠራጣሪ ነው ተብሏል፡፡
ቀደም ሲል በኢሜሬትስ ስታዲየም በተደረገው የመጀመሪያ ዙር የሩብ ፍፃሜ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ሁለት አቻ መለያየታቸው ይታወሳል።
በተመሳሳይ በሳንቲያጎ ቤርናባኦ ተገናኝተው ሶስት አቻ የተለያዩት ማንቸስተር ሲቲና ሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት የመልስ ጨዋታቸውን በኢቲሃድ ስታዲየም ያደርጋሉ።
በማንቸስተር ሲቲ በኩል ተካላከዩ ካይል ዎከር ከጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ ሲመለስ፤ ኬቨን ዲቡረይና እና ናታን አኬም በቡድኑ ስብስብ ውስጥ ሊካተቱ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
በሪያል ማድሪድ በኩል ደግሞ ግብ ጠባቂው ቲቦ ኮርቱዋ እና የመሀል ተከላካዪ ዴቪድ አልባ በጉዳት እንዲሁም የመሀል ክፍል ተጨዋቹ ኦርሊየን ሹዋሚኒ በቅጣት በዛሬው ጨዋታ እንደማይሰለፉ ተረጋግጧል፡፡