Fana: At a Speed of Life!

በሰሜናዊ ጅቡቲ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ የ38 ፍልሰተኞች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ የ38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ህይወት አልፏል፡፡

አደጋው የተከሰተው በትናንትናው ዕለት በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ ጎዶሪያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ሲሆን ÷60 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ በመገልበጧ 38 ፍልሰተኞች ባህር ውስጥ ሰጥመው ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የኢምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት በጀልባ መስጠም አደጋ ብቻ የ189 ኢትዮጵያውያን ሕይወት ማለፉ ተመላክቷል፡፡

በየጊዜው የሚደርሰው አደጋ መሻሻል ባይኖረውም የፍልሰተኞቹ ቁጥር ግን አሁንም እየጨመረ መምጣቱም ነው የተነገረው።

ከጅቡቲ የመን መስመር የሚደረግ ሕገ ወጥ ጉዞ ከፍተኛ የሞት ቁጥር እያስመዘገበ ያለ አደገኛ ጉዞ መሆኑ የገለጸው ሚሲዮኑ÷ዜጎች በህገ ወጥ ደላሎች ከመታለል እንዲቆጠቡና የፍትህ አካላትም ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.