በመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ፣ አሳግርት ወረዳ የጊና-ሀገር ከተማ እና በሐራ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ፣ አሳግርት ወረዳ የጊና-አገር ከተማ እና በሰሜን ወሎ ሐራ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
የድጋፍ ሰልፉ ባለፉት ዓመታት በለውጡ መንግሥት የመጡትን የማህበራዊ፣ ፖሊቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለመደገፍ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በለውጡ ዓመታት ላሳየው እመርታ ድጋፍ ለመግለጽ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በድጋፍ ሰልፉ በፅንፈኞችና ተላላኪዎች ምክንያት የሚፈርስ ክልልም መንግስትም የለም፣ ሀገራችንን ለማስቀጠል ከለውጡ አመራር ጎን እንቆማለን፣ ኢትዮጵያ ዳግም የአድዋን ድል እየደገመች ነው፣ ሰላማችን በእያንዳዳችን ቤት ናት የሚሉና ሌሎች ሀገራዊ አንድነት የሚያጠናክሩ መልእክቶች መተላለፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡