Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከጄ ኤስ አይ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የጄ ኤስ አይ የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ቢኒያም ደስታ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ በዚህ ወቅት ÷ ጄ ኤስ አይ በኢትዮጵያ ክትባትና የቤተሰብ ጤና አገልግሎት ላይ ለነበረው ትብብር አመስግነዋል ፡፡

ከአጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት ውይይት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው÷በጄ ኤስ አይ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችን ሚኒስቴሩ በ2030 ለማሳካት ካቀዳቸው ዘላቂ የጤና የልማት ግቦች ጋር ማናበብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ዶክተር ቢኒያም ደስታ በበኩላቸው ÷ድርጅታቸው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር  በተለዩ ዘርፎች ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ድርጅቱ በኢትዮጵያ በርካታ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ማድረጉን ያስረዱት ተወካዩ ÷ አሁን ላይም ከ15 በላይ ፕሮጀክቶችን እየተገበረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ጄ ኤስ አይ ጥራት እና ተደራሽነት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማዳረስ፣ ዘርፉን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ በአቅም ግንባታ፣ በድንገተኛ የጤና ስጋት ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም ድጋፍ እያደረገ መሆኑን  ጠቁመዋል፡፡

በውይይቱ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ክትባት አቅርቦትን ከማዳረስ አኳያ  በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር መደረጉንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.